Saturday, 16 April 2016

ከዛፍ ከድንጋይና ከመሳሰሉ ነገሮች በረከትን መፈለግ


ከዛፍ ከድንጋይና ከመሳሰሉ ነገሮች በረከትን መፈለግ

በረከትን መፈለግ ሸሪዓው ከፈቀደው እና ካልፈቀደነው ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ ሸሪዓው ከሚፈቅዳቸው ነገሮች ለምሳሌ ከቁርዓን በመካ በመዲናና በበይተል መቅዲስ ከመስገድ በረከት ለማብዛት መጣር የተወደደ ተግባር ሲሆን ሸሪዓው ከማይፈቅዳቸው ነገሮች ግን ለምሳሌ ከዛፍ ከድንጋይና ከቀብር በረከትን መፈለግ ሽርክ ነው፡፡

አቡ ዋቂድ አልለይሢይ እንዲህ ብለዋል፡-

አዲስ ሰለምቴዎች ሳለን ከነብዩ   ጋር ወደ ሁነይን ስንሄድ አጋሪዎች እርሱ ዘንድ በመቀመጥና መሳሪያቸውን ላዩ በማንጠልጠል በረከትን የሚፈልጉበት ዛፍ ነበራቸውና በአንዲት ዛፍ ስናልፍ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ እነሱ የሚያንጠለጥሉባት ዛፍ እንዳለቻቸው ሁሉ ለኛም ማንጠልጠያ ዛፍ አድርጉልንአልናቸው፡፡

የአላህ መልዕክተኛም በቁጣ እንዲህ አሉአላሁ አክበር! ይህ የተለመደ መንገድ ነው ነፍሴ በእጁ ባለችው እምላለሁ የኢስራኤል ልጆች ለሙሳ እንዲህ ያሉትን አይነት ነው ያላችሁት፡

اجْعَل لَّنَا إِلَهًا كَمَا لَهُمْ آلِهَةٌ  قَالَ إِنَّكُمْ قَوْمٌ تَجْهَلُونَ

ለነርሱ አማልክት እንዳሏቸው ለኛም አምላክን አድርግልን አሉት፤ እናንተ የምትሳሳቱ ህዝቦች ናችሁ አላቸው” (አል አዕራፍ)
 "ከበስተፊታችሁ የነበረን መንገድ ትከተላላችሁ”  

በዚህ ሀዲስ ከዛፍ በረከትን የፈለጉትን ሰዎች ሌላ አምላክ ከፈለጉ ሰዎች ጋር ማመሳሰላቸው የሚያመለክተው ከእንደዚህ አይነት ነገሮች በረከትን መፈለግ ማጋራት እንደሆነ ነው::


http://www.facebook.com/emnetihintebiq

Thursday, 14 April 2016

የአላህ ስሞችና ባህሪዎችን አስመልክቶ የዚህ ኡማህ አበው ትውልዶች (ሰለፉሳሊህ) እና የታላላቅ ኢማሞች አካሄድ


የአላህ ስሞችና ባህሪዎችን አስመልክቶ የዚህ ኡማህ አበው ትውልዶች (ሰለፉሳሊህ) እና የታላላቅ ኢማሞች አካሄድ

قال شيخ الإسلام ابن تيمية: "وطريقة سلف الأمة وأئمتها: أنهم يصفون الله بما وصف به نفسه وبما وصفه به رسوله مِنْ غَيْرِ تَحْرِيفٍ وَلا تَعْطِيل، وَلا تَكْييفٍ وَلا تَمْثِيل، إثبات بلا تمثيل، وتنزيه بلا تعطيل، إثبات الصفات، ونفي مماثلة المخلوقات، قال تعالى: {لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ} فهذا رد على الممثلة {وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ} الشورى: 11 رد على المعطلة." منهاج السنة 2/523

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ብለዋል፡ {የዚህ ኡማህ ቀዳሚ ትውልዶች (ሰለፎች) እና ታላላቅ ኢማሞች አካሄድ፡- አላህ እራሱን በገለጸባቸው እና መልዕክተኛው እርሱን በገለጹባቸው ባህሪዎች አላህን ይገልጹታል፤ ይህንን ሲያደርጉም፤ ያለተህሪፍ” (ትርጉም ማዛባት) እና ያለተዕጢል” (ትርጉም አልባ ማድረግ) እንዲሁም ያለተክዪፍ” (የባህሪዉን ሁኔታና ምንነት መግለጽ) እና ያለተምሢል” (አምሳያ ማድረግ) ነው፤ ባህሪዎችን ሲያጸድቁ አያመሳስሉም፤ አላህን ከአምሳያና ከጉድለት ባህሪዎች ሲያጠሩም ባህሪዎችን ትርጉም አልባ አያደርጉም፤ ከፍጡራን ጋር ያለን መመሳሰል ውድቅ በማድረግ ባህሪዎችን ማጽደቅ ነው መንገዳቸው።

አላህ እንዲህ ይላል፦
لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ} الشورى: ١١}

‹‹የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡›› (አል ሹራ 11)
«የሚመስለው ምንም ነገር የለም» የሚለው ክፍል አላህን ከፍጥረታቱ ጋር ለሚያመሳስሉሙሸቢሀዎችመመሳሰል እንደሌለ ምላሽ ይሰጣል።

«እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡›› የሚለው ክፍል ደግሞ ባህሪዎችን ለሚያስተባብሉለሙዓጢላዎችለአላህ የተገቡ ባህሪያት እንዳሉት ምላሽ ይሰጣል።} ሚንሀጁ ሱናህ ቅጽ ገጽ 523

ይህንን ለማረጋገጥ እና ለማመሳከር ይረዳ ዘንድ ታላላቅ አሊሞች እና የመዝሀብ መሪዎች እምነት ምን እንደሚመስል ከራሳቸው ንግግሮች የተወሰዱ ዘገባዎች ተሰብስበው በዚህ ክፍል መጨረሻ ላይ ሰፍረዋል። የአህሉሱና ተጻራሪ የሆኑት ጀህሚያና ሙዕተዚላ ወይም አሻዒራ የተባሉት ቡድኖች በጽሁፎቻቸው፤ «አመለካከታችንን የሚደግፍ የኡለማዎች የአቋም ስምምነት ወይምኢጅማዕአለ» ሲሉ የራሳቸውን ኡለማዎች የውስጥ ስምምነት ለመግለጽ እንጂ የሰለፎችን ኢጅማዕ ለማለት እንዳልሆነ ልብ ማለት ያስፈልጋል። አቋማቸው ከሰለፎች አቋም የተለየ እንደሆነ እና ከሰለፎች አቋም በተቃራኒው በዕውቀት እና በጥበብ የተሞላ እንደሆነ በድፍረት ይናገራሉ፡፡ ሱና የአንድነት መሰረት እንደሆነው ሁሉ ቢድዓ የልዩነት መንስኤና ምክንያት ነውና የሱና ተጻራሪዎች ብዙዉን ጊዜ በመሀከላቸው ስምምነት አይኖርም። ብዙዉን ጊዜአጅመዓ አስሀቡና” “የእኛ ባልደረቦች በዚህ ተስማምተዋልበማለት ነው የሚገልጹት። የኡለማዎቻቸው ኢጅማዕ እንዳለበት በዚህ መልኩ የሚናገሩበት ጉዳይ እንኳ ሲፈተሽ፤ ብዙዉን ጊዜ ስምምነቱ ትክክል እንዳልሆነ በሚያሳይ መልኩ እነርሱ ዘንድ ከተከበሩና ንግግራቸው ቦታ ካለው ኢማሞቻቸው እንዳልተስማሙበት ግልጽ ይሆናል። የአህሉሱና ተጻራሪዎች፤ ወጣ ላለው አቋማቸው እንኳን የሰለፎችን አቋም ሊያቀርቡ ቀርቶ የራሳቸዉን ኡለማዎች ስምምነት እንኳ ማቅረብ አይችሉም።


ስለዚህ ሀቀኛውን የአህሉሱና መንገድ በመከተል ሰሀቦች እና ታቢዒዮች የነበሩበትን እምነት ለመያዝአላህና መልዕክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ያረጋገጡትን ስምና ባህሪዎች ስናፀድቅ ከላይ የተጠቀሱትን አራት የጥመት በሮች መዝጋት የግድ ይላል።