Wednesday, 6 April 2016

የአላህ ባህሪዎችን በተመለከተ ለብዥታዎች መነሻ ከሆኑት ውስጥ በጥቂቱ:


የአላህ ባህሪዎችን በተመለከተ ለብዥታዎች መነሻ ከሆኑት ውስጥ በጥቂቱ:

ይህ የተውሂድ ክፍል ቀላልና ግልፅ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ብዙ የሙስሊም ቡድኖች ለቁርዓንና ለሀዲስ መረጃዎች እጅ ባለመስጠታቸዉና አጉል ፍልስፍናን በመጠቀማቸው ከትክክለኛው መንገድ ሲያፈነግጡና የተምታቱ ሀሳቦችን ሲያራምዱ ይስተዋላል፡፡ 

ከፊሎቹ የአላህን ባህሪዎች የተመለከቱ መረጃዎች፤ አላህን ከፍጡራን ጋር ስለሚያመሳስሉ አንቀበላቸውም ይላሉ፤ የተለየ ትርጓሜ በመስጠትም መልዕክታቸውን ያዛባሉ። መረጃዎቹን ተቀብሎ ማጽደቅም አላህን ከፍጡራን ጋር ማመሳሰል እንደሆነ ያስባሉ። ከዚህም አልፈው የሀቅ ባለቤቶች በኩፍር ይፈርጃሉ።

ሌሎች ደግሞአላህ በምናውቀው ቋንቋ ነውና የሚያናግረን በቁርዓንና በሀዲስ የአላህን ባህሪዎች የተመለከቱ መረጃዎችን የምንረዳው ፍጡራን ላይ ባወቅነው ትርጉም ብቻ ነውበማለት የአላህ ባህሪዎች ልክ እንደ ፍጡራን ባህሪዎች እንደሆኑ ይገልጻሉ። መረጃዎችን ከማየታቸው በፊት አላህ ፍጡራኑን እንደማይመስል እና ከፍጡራኑም እርሱን የሚመስል እንደሌለ የሚያስረዱ መረጃዎችን ቢያጤኑ ኖሩ ለዚህ ስህተት ባልተዳረጉ ነበር።

የሚከተለው ምሳሌ በዚህ ጉዳይ ላይ የሰዎች ውዝግብ ምንን መነሻ እንዳደረገ የምናይበት ነው።

የአላህን ከዓርሽ በላይ መሆን በተመለከተ፤ አላህ እንዲህ ብሏል፦

الرحمن على العرش استوى

አረህማን ከዐርሽ በላይ ከፍ አለ (ሆነ)” (ጣሃ 5)

አንዳንድ ቡድኖችአላህ ከዓርሽ በላይ ነውየሚሉ ሰዎች ለአላህ የፍጡራንን ባህሪ ስለሰጡካፊር ናቸውበማለት ይናገራሉ። በእነርሱ አመለካከት አንድ ሰውአላህ ከዓርሽ በላይ ነውካለ አንድ ፍጡር ከሌላ ፍጡር በላይ እንዲሆን የሚያስፈልጉት ነገሮች ሁሉ ያስፈልጋሉ። የአላህን ከዓርሽ በላይ መሆንኢስቲዋዕፍጡራን ከነገሮች በላይ ከመሆናቸው ጋር መለየት አልቻሉም። ስለዚህም የፈጣሪን ኢስቲዋዕ የተቀበለና ያመነ ሁሉ እነርሱ ቀድመው በአዕምሯቸው የቀረጹትን ምስል እንደተቀበለ አድርገው በማቅረብካፊር ነውይላሉ። ከእነዚህ ሰዎች መካከል ከፊሎቹ ስሞችንና ባህሪዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን ሁሉ በማጣመም ትርጉም አልባ አደረጓቸው። ስለዚህም «የአላህን ስሞችና ባህሪዎች ትክክለኛ ትርጉም አልባ አድራጊዎች» ‘‘ሙዓጢላህ’’ ተባሉ። ከእነርሱ መካከል ከፊሎቹ ደግሞ እነዚህን መረጃዎች አይተረጎሙም፤ በሌላ በማይታወቅ ቋንቋ እንደተነገሩ ታስበው እንዲሁ ይታለፋሉ፤ በማለት በአዕምሯቸው ከሳሉት ጣዖት ለማምለጥ ሞከሩ። እነዚህ ደግሞ «የአላህ ስሞችና ባህሪዎች ትርጉም አይታወቅም ባዮች» “ሙፈዊዳህተብለው ተሰየሙ። እነዚህ ቡድኖች ባህሪዎችን አያጸድቁም ነገር ግን አቋማቸውን ሲያስረዱ ከሰለፎች አቋም ጋር ለማመሳሰል ጥረት ስለሚያደርጉ ብዙ ሰዎችን ሊያምታቱ ይችላሉ። ሰለፎች የባህሪዎችን ትርጉም ያጸድቃሉ፤ ትርጉሙ አይታወቅም የሚሉት የባህሪዎችን ምንነትከይፊያብቻ ነው።

ሌሎች ደግሞ የአላህን ከዓርሽ በላይ መሆን ይቀበላሉ። ይሁንና የአላህን ከዓርሽ በላይ መሆን የሚረዱት ልክ ፍጡር ከፍጡር በላይ እንደሚሆነው ነው። ስለዚህምአላህ ከዓርሽ በላይ ነውስንል ልክሰው ዙፋን ላይ እንደሚቀመጠው ነውበማለት ያብራራሉ። እነዚህ ፈጣሪን «ከፍጡራን ጋር አመሳሳዮች» “ሙሸቢሀወይምሙመሲላይባላሉ።

የአማኞች ጋሻ”
‪#አስማዕወሲፋት

የፌስ ቡክ ገፃችንን ላይክ ያድርጉ

ሼር ማድረግም እንዳይረሱ

No comments:

Post a Comment