በዚህ ርዕስ ላይ የአህሉሱና አቋም ሶስት አጠቃላይ መርሆዎችን መሰረት ያደረገ ነው። እነዚህ መርሆዎችም በአላህ ስሞችና ባህሪዎች ዙሪያ የተስተካከለ አቋም እንዲኖር ይረዳሉ፡፡
الأصل الأَوّل : تَنزِيهُ اللهِ جَلَّ وَعَلاَ عَنْ أَنْ يَشْبَهَ شَيءٌ مِنْ صِفَاتِهِ شَيئًا مِنْ صِفَاتِ المَخْلُوقِين
የመጀመርያው መርሆ፡ ሁሉም የአላህ ባህሪዎች ከፍጡራን ባህሪዎች ጋር ፍጹም እንደማይመሳሰሉ በማመን አላህን ማጥራት “ተንዚህ” ፡፡
የመጀመርያው መርሆ፡ ሁሉም የአላህ ባህሪዎች ከፍጡራን ባህሪዎች ጋር ፍጹም እንደማይመሳሰሉ በማመን አላህን ማጥራት “ተንዚህ” ፡፡
الأصل الثّاني:الإيمانُ بمِاَ سَمَّى وَوَصَفَ اللهُ بِهِ نَفْسَهُ وَبِمَا سَمَّاهُ وَوَصَفَهُ بِهِ رِسُولُهُ صَلّى اللهُ عَلَيهِ وَسَلَّم عَلى الوَجهِ اللَّائِقِ بِجَلَالِ اللهِ وعَظَمَتِهِ
ሁለተኛው መርሆ፡ አላህ እራሱን በሰየመባቸው ስሞችና በገለፁባቸው ባህሪዎች፤ እንዲሁም መልዕክተኛውه አላህን በሰየሙባቸው ስሞችና በገለፁባቸው ባህሪዎች፤ ከአላህ ታላቅነትና ልዕልና ጋር በሚሄድ መልኩ ማመን፡፡
ሁለተኛው መርሆ፡ አላህ እራሱን በሰየመባቸው ስሞችና በገለፁባቸው ባህሪዎች፤ እንዲሁም መልዕክተኛውه አላህን በሰየሙባቸው ስሞችና በገለፁባቸው ባህሪዎች፤ ከአላህ ታላቅነትና ልዕልና ጋር በሚሄድ መልኩ ማመን፡፡
الأصل الثّالث: قَطْعُ الطَّمَعِ عَن إِدْرَاكِ حَقِيقَةِ كَيفِيَّةِ صِفَاتِ اللهِ لِأَنَّ إِدْرَاكَ المَخْلُوقِ لِذَلِكَ مُسْتَحِيلٌ
ሶስተኛው መርሆ፡ ፍጡራን የአላህን ባህሪዎች «ከይፊያ» ማወቅ ስለማይቻሉ፤ ይህንን ለማወቅ የሚኖርን ውስጣዊ ጉጉትና መቋመጥ መግታት፡፡
ሶስተኛው መርሆ፡ ፍጡራን የአላህን ባህሪዎች «ከይፊያ» ማወቅ ስለማይቻሉ፤ ይህንን ለማወቅ የሚኖርን ውስጣዊ ጉጉትና መቋመጥ መግታት፡፡
እነዚህን ሶስት መሠረቶች ያረጋገጠ በአላህ ስሞችና ባህሪዎች ትክክለኛ የሆነውንና ከጥንት ጀምሮ የኖሩ ታላላቅ የኢስላም ሊቃዉንት ያፀደቁትን እምነት አረጋግጧል ማለት ነው፡፡
☞ “የአማኞች ጋሻ”
#አስማዕወሲፋት
#አስማዕወሲፋት

No comments:
Post a Comment