የሰው ልጆች ሁሉ ሲፈጠሩና ወደዚህች ዓለም ሲመጡ አላህ ለባሪያዎቹ የመረጠውና የወደደውን የኢስላማዊ አቂዳ እምነት ይዘው ነው፡፡ ነገር
ግን ሸይጧን ከእነ ሰራዊቱ ከዚህ የቀና የእምነት ጐዳና በማስወጣት በአስከፊ የባዕድ አምልኮና ሽርክ ውሰጥ እንዲዘፈቁ አድርጓቸዋል፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ
ዐለይሂ ወሰለም) ይህንን በተመለከ በአስተላለፉት ሀዲስ፡-
የሀዲሱ አስላላፊ አቡ ሁረይራ በዚህ ዘገባ መጨረሻ ላይ፡-
“ከፈለጎችሁ የሚከተለውን የቁርአን አንቀፅ አንብቡ፤-
(( … የአላህን ፍጥረት ያቺን አላህ ሰዎችን በአርስዎ ላይ የፈጠረባትን (ሃይማኖት ያዙዋት)
የአላህን ፍጥረት እና (ሃይማኖት) መለወጥ የለም፣ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው፤ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡” (አል ሩም 3ዐ)
(ቡኻሪ ዘግበውታል)
ከአባታችን አደም ዘመን
አንስቶ እስከ ነብዩላሂ ኑህ ዘመን ድረስ የነበሩት ሕዝቦች በዚህ የአቂዳ እምነት ጐዳና በቀጥተኛነት ይጓዙ እንደነበር በቁርአንና
በሐዲስ ውስጥ በበርካታ አንቀጾች ተገልጿል፡፡ የተለያዩ ሰሃባዎች ንግግሮችም ይህንኑ ያረጋግጣሉ፡፡
ከእነዚህ የቁርአን ማስረጃዎችም
በአል-በቀራህ ቁጥር 213 ላይ አላህ እንዲህ ይላል፡-
‹‹ሰዎቹ ሁሉ አንድ ሕዝብ ነበሩ፤ (ተለያዩ)፡፡ አላህም ነቢያትን አብሳሪዎችና
አስፈራሪዎች አድርጎ ላከ፡፡››
(አል በቀራህ 213)
ፔጁን ላይክ ያድርጉ!
www.fb.com/emnetihintebiq
No comments:
Post a Comment