2ኛ. ሁለተኛው
የሽርክ አይነት ትንሹ
ሽርክ ነው፦
ትንሹ ሽርክ
ማለት ማንኛውም ወደ ትልቁ
ሽርክ መዳረሻ መንገድ የሆነ
ወይም ደግሞ ሸሪዓዊ ጥቅሶች ላይ
ሽርክ ተብሎ የተሰየመና ነገር ግን
የትልቁን ሽርክ መጠን
ያልደረሰ ሲሆን ነው፡፡
ይህ ሽርክ
በስራዎች ሁኔታና በምላስ
ንግግር የሚከሰት ሲሆን
ሸሪዓዊ ብይኑ ይህን
የሰራ ሰው ልክ እንደ ትላልቅ ወንጀሎች ፈፃሚ
በአላህ ፈላጐት ስር
ይሆናል፡፡
ለትንሹ ሽርክ
ምሳሌ ሊሆኑ ከሚችሉ ነገሮች፦
ሀ. ትንሹ
“ሪያእ” (ለይዩልኝ
መስራት)፡-
ለዚህ ማስረጃው
ኢማም አህመድና ሌሎችም ከነብዩ
የዘገቡት የሚከተለው ሀዲስ
ነው፦
‹‹እናንተ ላይ
ከምፈራው ሁሉ የከፋው
ትንሹ ሽርክ ነው፡፡ ሰሃቦችም “ትንሹ
ሽርክ ምንድ ነው?” ሲሉ ነብዩም
“መልካም ስራን ለይዩልኝ
መስራት ነው”
የትንሳኤው እለት
አላህ ለሰዎች ምንዳን ሲሰጥ
ለይዩልኝ ሚሰሩትን እንዲህ
ይላቸዋል
“በዱንያ ላይ
እንዲያዩላችሁ የምታደርጉት የነበሩ
ሰዎች ዘንድ ሂዱና እስቲ የሚሰጡዋችሁ ምንዳ ካለ
እዩ፡፡”
ለ. “በአላህና
በአንተ ፍላጐት…” የሚለው
አባባል፡-
አቡ ዳውድ
እንደዘገቡት ነብዩ እንዲህ
ብለዋል
‹‹በአላህና
በእገሌ ፍላጎት (ይህ
ጉዳይ ተሳካልኝ) አትበሉ:: ነገር
ግን አላህ ፍላጎት በኋላ እገሌም
ስለሻው…… ማለት ትችላላችሁ”
መ. “አላህና
እገሌ ባይኖሩ ኖሮ… ”
ወይም “ውሻ
ባይኖር ሌላ ገብቶ
ነበር” የመሳሰሉ ቃላቶችን መጠቀም፡፡
አቡ ሃቲም ተፍሲር መፅሐፋቸው ላይ
እንደዘገቡት ኢብኑ ዓባስ
ስለዚህ አንቀፅ ትርጉም
እንዲህ ብለዋል ፡-
فَلَا تَجْعَلُوا
لِلَّهِ أَندَادًا وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
‹‹ቢጤ
ማለት ተጋሪ ማለት ነው፡፡ የጉንዳን ኮቴ
በሌሊት ጨለማና በልሙጥ
ጥቁር ድንጋይ ላይ ስውር
ከሚሆነው በላይ ስውር
ነው፡፡
ለምሳሌ በአላህ
በህይወትህና በህይወቴ እምላለሁ
፣
==> ውሻ ባይኖር
ሌባ ይገባ ነበር ፣
==> ቤት ውስጥ
ዶሮ ባይኖር ሌባ ይገባ
ነበር ፣
==> በአላህና በአንተ
ፍላጐት ፣
==> አላህና አንተ
ባትኖሩ ኖሮ
የመሳሰሉትን ቃላት
መጠቀም ማለት ነው፡፡
“እገሌ” የገባበት ሁሉ ሽርክ
ነው፡፡ ብለዋል››
አላህ በእርሱ
ላይ እያወቁ ከማጋራት ይጠብቀን
ባለማወቅ በሰራነውም ይቅር
ይበለን!!!
No comments:
Post a Comment