ተውሒድ አል ኡሉሒያህ
ተውሒዱል ኡሉሒያ ማለት አምልኮዎች ሁሉ ለአላህ ብቻ እንደሚገቡና አጋር እንደሌለው በማመን አላህን ብቻ ማምለክ ነው፡፡
ተውሒዱል ኡሉሒያ ማለት አምልኮዎች ሁሉ ለአላህ ብቻ እንደሚገቡና አጋር እንደሌለው በማመን አላህን ብቻ ማምለክ ነው፡፡
ይህ የተውሂድ ክፍል ሰዎች የተፈጠሩለትና ሁሉም መልዕክተኞችም የተላኩበት ዋና አላማ ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ
وَالْإِنْسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
“ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም” (ዛሪያት 56)
وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ
رَسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ
‹‹በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፡፡ (ነህል 36)
وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ
مِنْ رَسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا أَنَا
فَاعْبُدُونِ
“ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም”(አንቢያ 25)
أَنْ لَا
تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ
أَلِيمٍ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَى قَوْمِهِ إِنِّي لَكُمْ نَذِيرٌ
مُبِينٌ
“ኑህንም ወደ ህዝቦቹ በርግጥ ላክን (አላቸውም) ፦ እኔ ለናንተ ግልፅ አስፈራሪ ነኝ:: አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ ፤ እኔ በናንተ ላይ የአሳማሚን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለው” (ሁድ 25−26)
وَإِلَى عَادٍ أَخَاهُمْ هُودًا
قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُمْ مِنْ إِلَهٍ غَيْرُهُ إِنْ
أَنْتُمْ إِلَّا مُفْتَرُونَ
“ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን፡፡ «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ አላቸው” (ሁድ 50)
وَإِلَى ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا
قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُمْ مِنْ إِلَهٍ غَيْرُهُ
“ወደ ሰሙድም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፡፡ «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ምንም አምላክ የላችሁም አላቸው” (ሁድ 61)
የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት…
http://www.facebook.com/emnetihintebiq
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!
No comments:
Post a Comment