ከቀብር ጋር ተያያዥነት ያላቸው ክልክል ተግባሮች
የእስልምና የመጀመሪያዎቹ ዘመናት ላይ ቀብርን መጐብኘት ተከልከሎ ነበር፡፡ ምክንያቱም ከድንቁርና ህይወት በመላቀቅ እንግዳ ስለነበሩና የተውሂድን ወሰን ለመጠበቅ ሲባል ነበር:: ሰዎች እምነታቸውን ሲያሳምሩ ከፍተኛ ስፍራ ሲሰጡት፣ ማስረጃዎቹ ግልፅ ሆነው ልቦች ውስጥ ሲሰርፅና የሽርክ ውዥንብሮች ሲጋለፁ ቀብርን መጐብኘት ዓላማው ተገድቦ ተፈቀደ፡፡
ቡረይዳ ኢብን ሁሰይብ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል
‹‹ከዚህ በፊት ቀብርን እንዳትጐበኙ ከልክያችሁ ነበር አሁን ግን ጎብኙ፡፡››
አቡሑረይራ እንዳስተላለፉት ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል
‹‹ቀብርን ጐብኙ ሞትን ያስታውሳችኋል፡፡››
አቡ ሰዒድ አል ኹድሪይ እንዳስተላለፉትም የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል
‹‹ቀብርን መጐብኘት ከልክያችሁ ነበር አሁን ግን ጐብኙ ትምህርት ይሰጣችኃል፡››
አነስ ኢብኑ ማሊክም እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል
‹‹ቀብርን መጐብኘት ከልክያችሁ ነበር አሁን ግን ጐብኙ ምክንያቱም ልብን ያርሳል፣ አይንን ያነባል፣ አኺራን ያስታውሳል፡፡ ነገር ግን የተከለከለን ቃል እንዳትጠቀሙ፡፡››
ቡረይዳህ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ) ወሰለም ቀብር ሲጐበኝ እንዲህ እንዲባል አስተምረዋል፦
"السلام عليكم أهل الديار من المؤمنين والمسلمين وإنا إن شاء الله بكم لاحقون أسأل الله لنا ولكم العافية"
“አሰላሙ ዓለይኩም አሕለ ዲያር ሚነል ሙእሚኒነ ወልሙስሊሚን ወኢና ኢንሻ አላሁ ቢኩም ላሂቁን አስአሉ ላሐ ለና ወለኩሙል ዓፊያ”
ትርጉሙ፦
(የአካባቢው ምእመናንና ሙስሊም ህዝቦች ሆይ! ሰላም በእናንተ ላይ ይስፈን እኛም በአላህ ፈቃድ ተከታዮቻችሁ ነን፡፡ አላህ እኛንም እናንተንም እንዲጠብቅ እለምናለው፡፡”
እነዚህና መሰል ሀዲሶች እንደሚጠቁሙት ቀብርን መጐብኘት ክልከላው ተነስቶ ለሁለት ታላላቅ ዓላማዎች ሲባል እንደተፈቀደ ነው፡፡
አንደኛ፡- አኺራን፣ ሞትንና ማለቅን በማስታወስ ዱንያን ችላ ለማለት እንዲሁም በቀብር ሰዎች ትምህርት በመውሰድ እምነትን ለማጠናከርና ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት በማሳመር ቸልተኝነትን ለማስወገድ፡፡፡
በሌላ በኩል ከቀብርና ከጉብኝቱ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ነገሮችን ሐዲስ ለተውሂድ ድንበር ጥበቃ ሲል ከልክሏል እነዚህን ማንኛውም ሙስሊም ከጥመት ለመጠበቅ ሲል ሊያውቃቸው ይገባል፡፡
No comments:
Post a Comment