አላህ
ከአርሽ በላይ ስለመሆኑ የኢማም
ማሊክ ድንቅ ምላሽ
የአላህ
ከዓርሽ በላይ መሆንን
በተመለከተ፤ አላህ ከዓርሽ
በላይ መሆኑን ማመን ተፈጥሯዊ
እምነት እንደሆነ እና
በዚህ ላይ የሚነሱ ማምታቻዎችና ብዥታዎች
የፈጠራ ሰዎች መገለጫ
መሆናቸውን ታላቁ የነብዩ
ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም
መስጅድ አስተማሪ እና
የመዝሀብ መሪ የሆኑት
አል-ኢማም ማሊክ ኢብኑ አነስ ገልጸዋል። አለአንቀጹ ተጠይቀው
የመለሱት ምላሽ እንደሚከተለው
ይነበባል።
قال
الأمام مالك رحمه الله- و قد سئل عن قوله تعالى
(5:20) الرَّحْمَنُ
عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَى
كيف
استوى؟
فقال «الاستواء غير مجهول، والكيف غير معقول، و الإيمان به واجب، و السؤال
عنه بدعة.
الرَّحْمَنُ
عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَى
“አረህማን ከዐርሽ በላይ
ሆነ (ከፍ አለ)” (ጣሃ 5)
ኢስቲዋዕ
እንዴት እንደሆነ ተጠየቁ።
“አላህ ከዓርሽ በላይ ከፍ
ያለው እንዴት ነው?”
ተባሉ።
እርሳቸዉም እንዲህ
ብለው መለሱ፦
“የአላህ
ከዓርሽ በላይ መሆን
“ኢስቲዋዕ”
ለማንም ሰው ግልጽ
ነው። ‘እንዴት?’
የሚለው ጥያቄ በአዕምሮ
ምርምር የሚደረስበት አይደለም፤
ይህንንም ተቀብሎ ማመን
ግዴታ ነው፤ ስለዚህ መጠየቅ በዲን
ዉስጥ የመጣ ፈጠራ “ቢድዓ”
ነው” ።
ይህ
አሰር ሰሂህ ነው።
አል-ኢማም
አላላካዒይ “ሸርህ
ኡሱል ኢዕቲቃድ አህሊሱናህ”
በተባለው መጽሀፍ ቅጽ
2 ገጽ 398
[ዳሪሚይ
“አል ረድ
አለልጃህሚያህ” ገጽ
33 አልበይሀቂይ “አል
አስማዕ ወሲፋት”
ቅጽ 2 ገጽ 150-151]
[አቡ
ዑስማን አሷቡኒይ “ዓቂደቱሰለፍ” ገጽ
17-19 ኢብኑ አብድልበር “ተምሂድ” ቅጽ 7 ገጽ
151 ሌሎችም በስፋት ዘግበውታል።]
[ኢብኑ ሀጀርም በይሀቂይ ከ
አብዱላህ ኢብኑ ዋህብ
መልካም በሆነ ሰነድ
እንደተዘገበ ጽፈዋል(ቅጽ
13፡ ገጽ 407)።]
ይህንን
አሰር ዶክተር አብዱረዛቅ አልበድር
“አልአሰር አልመሽሁር
ዓኒል ኢማም ማሊክ ቢን አነስ” በተሠኘ
ድንቅ ጽሁፍ ሰነዱንና መለዕክቱን አብራርተዋል።
አል
ኢማም አዘሀቢይ «ይህ ከኢማም
ማሊክ የተገኘ ማጽደቅ “ኢስባት” ነው።
ልክ እንደዚሁ ከማሊክ ሽይኽ
ረቢዓህ ተዘግቧል። እንደዉም
የአህሉሱና ሁሉ ንግግር
ነው» ።
አላህ
ከአርሽ በላይ ነው!!!
የፌስ
ቡክ ገፃችንን ለማግኘት
https://m.facebook.com/emnetihintebiq
🔚ቢያንስ ለ3
ሰው ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!
No comments:
Post a Comment