Wednesday, 16 December 2015

ቁርኣን ስለ ሽርክ ምን አለ ???

አላህ በተከበረው ቃሉ ስለ ሽርክ ምን አለ???

በመጀመሪያ ሽርክ (ማጋራት) ማለት  ለአላህ ብቻ ከሚገቡ ነገሮች አንዱንም ቢሆን ከሱ ውጪ ለሆነ ፍጡር ማድረግ በመሆኑ የተውሂድ ተቃራኒ ነው፡፡
 አላህ እንዲህ ይላል፡-

وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا

አላህንም ተገዙ በርሱም ምንንም አታጋሩ

(አን ኒሳእ 36)

ሁለተኛ ሽርክ ከኃጢአቶች ሁሉ የከፋ ከበደሎቸ ሁሉ የላቀ ሲሆን አንድ ሰው ንሰሀ ሳይገባ በሽርክ ላይ እንዳለ ከሞተ ኃጢአቱ የማይማርና ጀነት እርም የሆነበት ሆኖ ጀሀነም ውስጥ ይዘወትራል፡፡

አላህ እንዲህ ይላል፡-

إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ

ማጋራት ታላቅ በደል ነው

 (ሉቅማን 13)

إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَى إِثْمًا عَظِيمًا

አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኃጢአት በእርግጥ ቀጠፈ::”

 (አል ኒሳህ 48)

إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَلِكَ لِمَن يَشَاءُ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا بَعِيدًا

አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው (ከውነት) የራቀን ጥመት በእርግጥ ጠመመ

(አን ኒሳእ 116)

إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ:: መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም::”

(አል ማአዳህ 72)

አላህ እኛንም ቤተሰቦቻችንን እንዲሁም ሙስሊሙን ዑማ ሁሉ ከዚህ አፀያፊና ከባድ ወንጀል ይጠብቀን::

No comments:

Post a Comment