Wednesday, 16 December 2015

የተውሂድ ጠቀሜታዎች

ርዕስ: ~ የተውሂድ ጠቀሜታዎች

http://www.facebook.com/emnetihintebiq

ተውሂድ ከዲን መሰረታዊ ከሆኑ ነገሮች በሙሉ ቅድሚያ ሊቸረው የቻለው አያሌ ጠቀሜታዎች ስላሉት ነው::
ከነዚህም መካከል የሚከተሉት የጎላ ጠቀሜታዎች ይገኛሉ::

1_ተውሂድ በዱንያም ሆነ በአኼራ ለሚከሰቱ ጭንቀቶችና ቅጣቶች መከላከያና መጠበቂያ ነው::

2_በልቦናው ውስጥ ቅንጣት ታክል እንኳ ተውሂድ ኖሮት ወንጀሎችን ፈፅሞ የአላህ  እዝነት  ሳያገኘው  ቀርቶ  እሳት ቢገባ ግለሰቡ እሳት  ውስጥ  ዘውታሪ  አይሆንም:: ነገር  ግን  ሙሉ  በሙሉ  ልቦናው  በተውሂድ  የተሞላ ከሆነ  በዱንያ  ከጥመት  የራቀ  ይሆናል  በአዀራ  ደግሞ  ሙሉ  ደህንነትን  ያገኛል (እሳት ከነጭራሹ አይገባም)::

3_ተውሂድ የአላህን ውዴታንና ምንዳውን ለማግኘት ብቸኛው ሰበብ ነው::

4_ ተውሂድን የያዘ ግለሰብ  ብዙ  አስከፊ  ነገሮች  ቢገጥሙትም እንኳ ከአላህ ውሳኔ መሆኑን በማመን በህይወቱ በጣም ደስተኛና የተረጋጋ ይሆናል::

5_ተውሂድን የያዘ ግለሰብ ለፍጠር ተገዥ ባሪያ አይሆንም::የሚፈራው:የሚከጅለው:ደጅ የሚጠናው ጌታን አንድ አላህን ብቻ ይሆናል::ይህ ነው የክብርና የልቅና መገለጫ!

6_ተውሂድን የያዘ ግለሰብ አላህ መጥፎ ከሚባል ነገር በሙሉ ሊጠብቀውና ጀነትን ሊያስገባው እንዲሁም በዚህች አለም እርሱን በማውሳት የመንፈስ እርካታን ሊያጎናፅፋቸው ቃል ገብቷል::


አላህ እርሱን በብቸኝነት ማምለክን ያጎናፅፈን ጀነቱንም ይወፍቀን!!!

No comments:

Post a Comment