Tuesday, 2 February 2016

አምልኮ (ዒባዳ)

አምልኮ (ዒባዳ)

ዒባዳ አላህ ለሚወዳቸው ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ ንግግሮች እና ተግባሮች ሁሉ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ የአምልኮ ዓይነቶች ብዙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ሰላት፣ ሩኩዕ፣ ሱጁድ ፣ እርድ(ዘብህ) ፣ ኹሹእ(መተናነስ)፣ መመካት፣ዱዓእ፣ፍራቻ(ኸዉፍ)፣ተስፋ ማድረግ (ረጃዕ)፣ ጠዋፍ እና መሐላ  እንዲሁም ሌሎች አላህ የደነገጋቸው የአምልኮ ዘርፎች ሁሉ ዒባዳ ይባላሉ፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ)) الأنعام: ١٦٢ 

(ስግደቴ አምልኮቴም ህይወቴም ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው በል)አል-አንዓም162
የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ)በሀዲሰል ቁድስ አላህ እንዲህ እንዳለ ይገልፃሉ                     ((ባሪያዬ እኔ ግዴታ ያደረግኩበትን ነገሮች ከመፈፀሙ በተሻለ ወደ እኔ የቀረበ የሚያደርገዉ ስራ የለም፡፡)) ቡኻሪ ዘግበዉታል
አላህ መልዕክተኞችን የላከው ወደ እርሱ አምልኮት እንዲጣሩና በእርሱ አምልኮ ላይ የሚፈፀም ሽርክን (ማጋራትን) እንዲያወግዙ ነው፡፡አላህ እንዲህ ይላል፡-
((وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ)) النحل: ٣٦
(በየህዝቡም ሁሉ ዉስጥ አላህን አምልኩ ጣዖትንም ራቁ በማለት መልዕክተኞችን በእርግጥ ልከናል) አል ነህል 36
የአምልኮ የሚገነባባቸው መሰረቶች ሶስት ናቸው፡-
አንደኛ፡- ለተመላኪው በሙሉ ልብ መውደድ፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
((وَالَّذِينَ آمَنُوا أَشَدُّ حُبًّا لِّلَّهِ)) البقرة: ١٦٥
‹‹እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡(አል በቀራህ 165)
ሁለተኛ፡- በሙሉ  ልብ መከጀል:: አላህ አንዲህ ይላል፡-
((وَيَرْجُونَ رَحْمَتَهُ )) الإسراء: ٥٧
‹‹እዝነቱንም ይከጅላሉ፡፡›› (አል ኢስራህ 57)
ሶስተኛ፡- በሙሉ  ልብ መፍራት:: አላህ እንዲህ ይላል፡-
((وَيَخَافُونَ عَذَابَهُ )) الإسراء: ٥٧
‹‹ቅጣቱንም ይፈራሉ፡፡››(አል ኢስራህ 57
     አላህ እነዚህን ሶስት ታላላቅ መሰረቶች በፋቲሃ ምዕራፍ እንዲህ በማለት አካቷቻዋል፡፡
((الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ * الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ *  مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ )) الفاتحة: ١ - ٤
‹‹ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤ እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ፡፡ የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡››(አል ፋቲሃ 1-3)
በመጀመሪያው አንቀጽ ውዴታ ተጠቅሷል፡፡ ምክንያቱም አላህ ባለ ውለታ ነው፡፡ ባለውለታ ደግሞ በዋለው ልክ ይወደዋል፡፡ በሁለተኛው አንቀጽ ክጀላ ተጠቁሟል፡፡ ሶስተኛው አንቀጽ ላይ ደግሞ ፍራቻ ተጠቅሷል፡፡ ምክንያቱም የምንዳና የመተሳሰብ ቀን ንጉስ ከቅጣቱ ይፈራል፡፡ ስለዚህም ነው አላህ በማስከተል እንዲህ ያለው  (إِيَّاكَ نَعْبُدُ) ማለትም የነዚህ ሶስቱ ባለቤት ጌታ ሆይ ይህ አንቀጽ         (الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ ) በሚጠቁመው ውዴታህ፣ ይህ አንቀጽ ( الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ )                       
በጠቆመው ክጀላህና ይህ አንቀጽ (مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ ) በጠቆመው ፍራቻህ አመልክሃለው ማለት ነው፡፡
አምልኮ በሁለት መሰፈርቶች እንጂ ተቀባይነት የለውም፦
1ኛ፡- አምልኮን ለተመላኪው ብቻ ለይቶ መስጠት፡፡ አላህ ለእርሱ ፊት ብቻ ጥርት የተደረገን ስራ እንጂ አይቀበልም፡፡ አላሀ እንዲህ ይላል፡-
((وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ )) البينة: ٥
‹‹የአላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት... እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)፡፡›› (አል በይነህ 5)
((أَلَا لِلَّهِ الدِّينُ الْخَالِصُ)) الزمر: ٣
‹‹ንቁ! ፍጹም ጥሩ የኾነው ሃይማኖት የአላህ ብቻ ነው፡፡›› (ዙመር 3)
((قُلِ اللَّهَ أَعْبُدُ مُخْلِصًا لَّهُ دِينِي )) الزمر: ١٤
አላህን «ሃይማኖቴን ለእርሱ ያጠራሁ ኾኜ እግገዛዋለሁ» በል፡፡ (ዙመር 14)
2ኛ፡- መልዕክተኛውን (ﷺ)  ተከታይ መሆን፡፡ አላህ ማንኛውም ስራ የመልዕክተኛውን (ﷺ)  መመሪያ ያልተስማማ ከሆነ አይቀበልም፡፡  አላህ እንዲህ ይላል፡-
((وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا )) الحشر: ٧
‹‹መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡›› (አል ሀሽር7)
((فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لَا يَجِدُوا فِي أَنفُسِهِمْ حَرَجًا مِّمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا تَسْلِيمًا )) النساء: ٦٥
‹‹በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም፤ (ምእመን አይኾኑም)፡፡››(አል ኒሳህ 65)


 ነብዩም (ﷺ)  እንዲህ ብለዋል
من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فـهو رد}
‹‹በዚህ ዲናችን ውሰጥ ከሱ ያልሆነን አዲስ ነገር የፈጠረ ስራው ተመላሽ ነው፡፡››
ለአላህ ብቻ በመለየት ያልተሰራና ትክክለኛ ያልሆነ ስራ ትርጉም የለውም፡፡
    እነዚህን ሁለት መስፈርቶች አካተው ከያዙ አንቀፆች ውሰጥ የሚከተለው በአል ከህፍ ምዕራፍ መጨረሻ ላይ የተወሳው የአላህ ቃል አንዱ ነው፡፡
((قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُو لِقَاءَ رَبِّهِ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًا صَالِحًا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا )) الكهف: ١١٠
«እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደኔ የሚወረድልኝ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ (አል ከህፍ 11)

No comments:

Post a Comment