Tuesday, 2 February 2016

የሩቅ ምስጢር አዋቂ ነን ባዮች ስራ!

የሩቅ ምስጢር አዋቂ ነን ባዮች ስራ!

1. ኮከብ ቆጠራ፡-   

ኮከብ ቆጠራ ማለት በኮከቦች ሁኔታ ምድር ላይ የሚከሰትን ነገር መተንበይ ማለት ነው፡፡
ኢብኑ ዓባስ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ () እንዲህ ብለዋል
 ‹‹ከከዋክብት እውቀት የተወሰነ የቀነጨበ ከድግምት የተወሰነን ቀነጨበ ማለት ነው:: በጨመረም ቁጥር ከድግምት ጨመረ ማለት ነው፡፡››

2. ወፍ ማባረርና መሬት ላይ ማስመር፡-

ቀጠን ኢብን ቀቢሳ ከአባቱ እንዳስተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ () እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው ብለዋል
 ‹‹ወፍ ማባረር፣ ገድ ማለትና መሬት ላይ ማስመር ከድግምት ነው››
=> ወፍ ማባረር ማለት ወፍ በመልቀቅ በአበራረሯና በሁኔታዋ ገድ ማለት ሲሆን
=> መሬት ላይ ማስመር ደግሞ መስመር በማስመርና ጠጠሮችን በመወርወር የሩቅን ምስጢር አውቀለሁ ባይነት ነው፡፡
 እነዚህ ሁሉ በጃሒሊያ ስርዓት የነበሩ ጥንቆላዎች ናቸው::

3. ጥንቆላ፡- 

ጥንቆላ የሩቅን ምስጢር አውቃለው ማለት ሲሆን መሠረቱ ጂኖች የመልአኮችን ንግግር መስረቅና ለጠንቋዩ ጆሮው ላይ ሹክ ማለት ነው፡፡
 አቡ ሑረይሪ እንደተላለፈው ነብዩ () እንዲህ ብለዋል
‹‹ወደ ጠንቋይ በመሄድ የሚለውን የተቀበለ ሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል››

4. የ “አባጃድ” ፊደሎችን መፃፍ፡-

ይህ ማለት ለፊደሎች ቁጥር በመስጠትና የሰዎችን የጊዜያትንና የቦታን ስም በመስጠት አንዱ እድለኛ ነው ሌላው እደለቢስ ነው የመሳሰሉትን እያሉ መፍረድ፡፡

 ኢብኑ ዓባስ “አባጃድ የሚፅፉና ከዋክብትን የሚቆጥሩ ሰዎችን በተመለከተ ይህን የፈፀመ አላህ ዘንድ ምንም እጣ ፈንታ የለውም እላለው” ብለዋል::

5. መዳፍንና የቡና ሲኒን ማንበብ፡-

ይህ አንዳንዶች መሞት፣ መኖር፣ ድህነት፣ ሀብት፣ ጤንነትና በሽታን የመሳሰሉትን የወደፊት ክስተት የሚተነብዩበት ነው፡፡

 6. ሟች ነፍስን ማናገር፡-

 የዚህ ተጠሪዎች ሰው ሲሞት ነፍሱን እንደሚያናግሩና እዚያ ያለውን ፀጋና ቅጣት የመሳሰሉት እንደሚያውቁ በሀሰት ይናገራሉ፡፡

7. በገድ ማመን፡-

በበራሪ ወፎችና በቀበሮ በመሳሰሉት ጩኸቶች ይህ ይቀናኛል ወይም አይቀናኝም እያሉ ገድ ማለት ሲሆን ይህ ሽርክና ሸይጧናዊ ማስፈራሪያ ነው፡፡
 ዒምራን ኢብኑ ሁሰይን እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ () እንዲህ ብለዋል

 ‹‹ገድ ያለ ወይም እንዲባልለት ያደረገ፣ የጠነቆለ ወይም የተጠነቆለለት፣ ድግምት የሰራ ወይም እንዲሰራለት ያደረገ ከእኛ አይደለም፤ ወደ ጠንቋይ በመሄድ የሚለውን አምኖ የሚቀበል ሙሐመድ ላይ በተወረደው ክዷል፡፡››

 አላህ የሙስሊሞችን ጉዳይ እንዲያሳምር፣ ሃይማኖታቸውን እንዲያስገነዝባቸውና ከሙጅሪሞችና ከሸይጧን ረዳቶች ተንኮል እንዲጠብቃቸው እንለምናለን፡፡




No comments:

Post a Comment