Tuesday, 2 February 2016

የአላህን ባህሪያት ስናጸድቅ ማወቅ የሚገባን ወሳኝ ገደቦች

የአላህን ባህሪያት ስናጸድቅ ማወቅ የሚገባን ወሳኝ ገደቦች
 የአላህ ስሞችና ባህሪዎችን ለማፅደቅ ትክክለኛው መንገድ አላህና መልዕክተኛው ያረጋገጡትን ያለ:-
“ተህሪፍ” (ትርጉሙ ሳይዛባ) ፣  ያለ “ተዕጢል”(ትርጉም የለሽ ሳይደረግ)፣  ያለ “ተክይፍ” (አይነቱ ሳይጠቀስ) እና ያለ  “ተምሢል” (አምሳል ሳይደረግለት) ማመን ነው፡፡
ተህሪፍ (ትርጉሙን ማዛባት)
   ተህሪፍ (ትርጉሙን ማዛባት) የተፈለገውን ትርጉም መቀየር ማለት ሲሆን በሁለት አይነቶች ይከፈላል፦
“ተህሪፉ ለፍዝ” (ቃሉን ማጥመም) ይህ የሚሆነው የቁርአን ወይም የሀዲስ ቃላቶች ላይ ሌላ ቃልን በመጨመር፣በመቀነስ ወይም አነባቡን በመለወጥ ነው፡፡ለምሳሌ :-
ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَٰﻦُ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟْﻌَﺮْﺵِ ﺍﺳْﺘَﻮَﻯ:طه :ه
 `ኢስተዋ` የሚለውን `ኢስተውላ` በሚል መቀየር:: (በዚህ... ሳቢያ አላህከ ዐርሽ ላይ በላይ ሆነ በሚል የሚሰጠውን ትርጉም ዐርሽን ተቆጣጠረ በሚል እንዲለወጥ ያደርጋል::)
 2. ተህሪፉል መዕና (ትርጉሙን ማጣመም) የቁርአንና የሀዲስን ቃሎች አላህ ባልፈለገው ትርጉም መተርጐም ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ “የድ” (እጅ) የሚለውን ሀይል ወይም ፀጋ በማለት ትርጉሙን መለወጥ:: እንዲህ አይነቱ ትርጓሜ ሸሪዓውም ሆነ ቋንቋው አይቀበሉትም፡፡

“ተዕጢል” (ትርጉም የለሽ ማድረግ)
  “ተዕጢል” (ትርጉም የለሽ ማድረግ) አላህ በምንም ባህሪ አይገለፅም ብሎ ማስተባበል ማለት ነው፡፡
በ”ተህሪፍ” እና በ”ተዕጢል” መካከል ያለው ለውጥ፡- “ተህሪፍ” ማስረጃዎች የሚደግፉትን ትክክለኛ ትርጉም በሐሰት ትርጉም መቀየር ሲሆን “ተዕጢል” ደግሞ ትክክለኛውን ትርጉም አግልሎ ያለ ተለዋጭ ትርጉም መተው ነው፡፡
“ተክይፍ” የባህሪውን ሁኔታና አይነት መወሰን
 “ተክይፍ” የባህሪውን ሁኔታና አይነት መወሰን ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ የአላሀ እጅ እንዲህ አይነት ነው፣ አላህ ዐርሽ ላይ ሲደላደል በእንዲህ አይነት ሁኔታ ነው በመሳሰሉት መልኩ መዘርዘር ማለት ሲሆን ይህ ተግባር ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም ከአላህ በቀር የእርሱን ባህሪ ሁኔታ የሚያውቅ የለም፤ ፍጡራን ይህን ማወቅ አይችሉም፡፡
“ተምሢል” የአላህን ባህሪያቶች ማመሳሰል
 “ተምሢል” የአላህን ባህሪያቶች ማመሳሰል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ የአላህ መስሚያ እንደኛ ነው፣ የእርሱ ፊት እንደኛ ፊት ነው ማለት ነው፡፡
የአላህ ስሞችና ባህሪዎችን አስመልክቶ ሶስት ዋና ዋና ነጥቦች
1- አላህ በቁርኣኑ ራሱን የገለፀባቸውን ወይም መልዕክተኛው በተረጋገጡ ዘገባዎች ላይ ያፀደቋቸውን የጌታችንን ስሞችና ባህሪያት በሙሉ እንዳሉ ተቀብሎ ማፅደቅ፤
2- በቁርኣንና በሐዲሥ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ውድቅ የተደረጉ ጉድለቶችን ሁሉ ውድቅ ማድረግ፤
3- በርዕሱ ላይ በቁርኣንና በሐዲሥ ያልተወሱ ቃላትንና ገለፃዎችን መልዕክታቸውን ሳያጣሩ አለመቀበል።


No comments:

Post a Comment